2 የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው።
3 እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፤ብርቱ ምሽግ እንደሆናት አስመስክሮአል።
4 እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ።
5 አይተውም ተደነቁ፤ደንግጠውም ፈረጠጡ።
6 ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣በዚያ ብርክ ያዛቸው።
7 የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣አንተ አብረከረክሃቸው።
8 እንደ ሰማን፣በሰራዊት አምላክ ከተማ፣በአምላካችን ከተማ፣እንዲሁ አየን፤እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ