1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤መቃተቴንም ቸል አትበል።
2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ድረስልኝ ብዬ ስጮህ ስማኝ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ፤
4 አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ክፉም ከአንተ ጋር አያድርም።
5 እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ።
6 ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።
7 እኔ ግን በምሕረትህ ብዛትወደ ቤትህ እገባለሁ፤አንተንም በመፍራት፣ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ።