12 ብራብ ለአንተ አልነግርህም፤ዓለምና በውስጧ ያለውም ሁሉ የእኔ ነውና።
13 ለመሆኑ፣ እኔ የኰርማ ሥጋ እበላለሁን?የፍየልንስ ደም እጠጣለሁን?
14 ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ለልዑልም ስእለትህን ስጥ።
15 በመከራ ጊዜ ወደ እኔ ጩህ፤አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”
16 ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤“ሕጌን ለማነብነብ፣ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ?
17 ተግሣጼን ትጠላለህና፤ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።
18 ሌባውን ስታይ አብረኸው ነጐድህ፤ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።