15 በመከራ ጊዜ ወደ እኔ ጩህ፤አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”
16 ክፉውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤“ሕጌን ለማነብነብ፣ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ?
17 ተግሣጼን ትጠላለህና፤ቃሌንም ወደ ኋላህ ትጥላለህ።
18 ሌባውን ስታይ አብረኸው ነጐድህ፤ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
19 አፍህን ለክፋት አዋልህ፤አንደበትህም ሽንገላን ጐነጐነ።
20 ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፤የእናትህንም ልጅ ስም አጐደፍህ።
21 ይህን አድርገህ ዝም አልሁ፤እንዳንተ የሆንሁ መሰለህ።አሁን ግን እገሥጽሃለሁ፣ፊት ለፊትም እወቅስሃለሁ።