4 በሕዝቡ ይፈርድ ዘንድ፣በላይ ያለውን ሰማይንና ምድርን እንዲህ ብሎ ይጠራል፤
5 “በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ኪዳን የገቡትን፣ቅዱሳኔን ወደ እኔ ሰብስቧቸው።”
6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤እግዚአብሔር ራሱ ፈራጅ ነውና። ሴላ
7 “ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ ልንገርህ፤እስራኤል ሆይ፤ በአንተ ላይ ልመስክር፤አምላክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
8 ስለ መሥዋዕትህ አልነቀፍሁህም፤የሚቃጠል መሥዋዕትህማ ሁል ጊዜ በፊቴ ነው።
9 እኔ ግን ኮርማህን ከበረት፣ፍየሎችህንም ከጒረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤
10 የዱር አራዊት ሁሉ፣በሺ ተራራዎች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና።