3 ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ
4 እነሆ፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፤ጌታም ደግፎ ይይዘኛል።
5 የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው።
6 በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ነውና፣ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤
7 ከመከራ ሁሉ ታድጎኛልና፤ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቶአል።