2 ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስልኝም።በውስጤ ታውኬአለሁ፤ ተናውጬአለሁም፤
3 በጠላት ድምፅ ተሸበርሁ፤በክፉዎች ድንፋታ ደነገጥሁ፤መከራ አምጥተውብኛልና፤በቍጣም ተነሣሥተው ጠላት ሆነውብኛል።
4 ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።
5 ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ሽብርም ዋጠኝ።
6 እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ!በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤
7 እነሆ፤ ኰብልዬ በራቅሁ፣በምድረ በዳም በሰነበትሁ ነበር፤ ሴላ
8 ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ፣ወደ መጠለያዬ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር።”