8 ሰቆቃዬን መዝግብ፤እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን?
9 ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ።
10 ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር፣
11 በአምላክ ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተ ስእለት አለብኝ፤የማቀርብልህም የምስጋና መሥዋዕት ነው፤
13 በሕያዋን ብርሃን፣በእግዚአብሔር ፊት እመላለስ ዘንድ፣ነፍሴን ከሞት፣እግሬንም ከመሰናክል አድነሃልና።