1 አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።
2 ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።
3 እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴበላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።
4 እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።