4 እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።
5 የሰራዊት አምላክ የሆንህ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ሕዝቦችን ሁሉ ለመቅጣት ተነሥ፤በተንኰላቸው በደል የሚፈጽሙትንም ሁሉ አትማራቸው። ሴላ
6 እንደ ውሻ እያላዘኑ፣በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።
7 ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤“ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ።
9 ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።
10 እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል።