6 እንደ ውሻ እያላዘኑ፣በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።
7 ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤“ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ።
9 ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።
10 እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል።
11 ጋሻችን ጌታ ሆይ፤ አትግደላቸው፤አለበለዚያ ሕዝቤ ይረሳል፤በኀይልህ አንከራታቸው፤ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው።
12 ከአፋቸው ስለሚወጣው ኀጢአት፣ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል፣በትዕቢታቸው ይያዙ።ስለ ተናገሩት መርገምና ውሸት፣