1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ጸሎቴንም አድምጥ።
2 ልቤ በዛለ ጊዜ፣ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።
3 አንተ መጠጊያዬ፣ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና።
4 በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ