12 ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን፤የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።
13 የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤
14 በመከራ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣በከንፈሬም የተናገርሁት ስእለት ነው።
15 ፍሪዳዎችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣አውራ በጎችንም የሚጤስ ቍርባን አድርጌ አቀርብልሃለሁ፤ኰርማዎችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ። ሴላ
16 እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።
17 በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤በአንደበቴም አመሰገንሁት።
18 ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ጌታ ባልሰማኝ ነበር።