6 ባሕሩን የብስ አደረገው፤ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ኑ፣ በእርሱ ደስ ይበለን።
7 በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ
8 ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
9 እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።
10 አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤እንደ ብርም አነጠርኸን።
11 ወደ ወጥመድ አገባኸን፤በጀርባችንም ሸክም ጫንህብን።
12 ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን፤የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።