2 መንገድህ በምድር ላይ፣ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
4 ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
6 ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
7 እግዚአብሔር ይባርከናል፤የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ይፈሩታል።