1 አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና።
2 የእግር መቆሚያ በሌለው፣በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ሞገዱም አሰጠመኝ።
3 በጩኸት ደከምሁ፤ጉሮሮዬም ደረቀ፤አምላኬን በመጠባበቅ፣ዐይኖቼ ፈዘዙ።
4 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ከራሴ ጠጒር በዙ፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ያልሰረቅሁትን ነገር፣መልሰህ አምጣ ተባልሁ።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
6 ጌታ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤የእስራኤል አምላክ ሆይ፤አንተን አጥብቀው የሚሹ፣ከእኔ የተነሣ አይዋረዱ።