10 ነፍሴን በጾም ባስመረርሁ ጊዜ፣እነርሱ ሰደቡኝ።
11 ማቅ በለበስሁ ጊዜ፣መተረቻ አደረጉኝ።
12 በቅጥሩ ደጅ ለሚቀመጡት የመነጋገሪያ ርእስ፣ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ።
13 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት፣ወደ አንተ እጸልያለሁ፤አምላክ ሆይ፤ በታላቅ ምሕረትህ፣በማዳንህም እርግጠኝነት መልስልኝ።
14 ከረግረግ አውጣኝ፤እሰጥም ዘንድ አትተወኝ፤ከጥልቅ ውሃ፣ከእነዚያ ከሚጠሉኝ ታደገኝ።
15 ጐርፍ አያጥለቅልቀኝ፤ጥልቅ ውሃም አይዋጠኝ፤ጒድጓዱም ተደርምሶ አይዘጋብኝ።
16 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ በጎ ናትና ስማኝ፤እንደ ርኅራኄም ብዛት መለስ በልልኝ።