24 መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤የቍጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው።
25 ሰፈራቸው ባድማ ይሁን፤በድንኳኖቻቸው የሚኖር አይገኝ፤
26 አንተ የመታኻቸውን አሳደዋልና፤ያቈሰልኻቸውንም ሥቃያቸውን አባብሰዋል።
27 በበደላቸው በደል ጨምርባቸው፤ወደ ጽድቅህም አይግቡ።
28 ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰሱ፤ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።
29 ነገር ግን እኔ በሥቃይና በጭንቅ ላይ እገኛለሁ፤አምላክ ሆይ፤ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ።
30 የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አወድሳለሁ፤በምስጋናም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።