33 እግዚአብሔር ችግረኞችን ይሰማልና፤በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም።
34 ሰማይና ምድር፣ ባሕርም፣በውስጣቸውም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመስግኑት።
35 እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፤የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና፤ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል፤ ይወርሳታልም።
36 የባሪያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል፤ስሙንም የሚወዱ በዚያ ይኖራሉ።