4 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ከራሴ ጠጒር በዙ፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ያልሰረቅሁትን ነገር፣መልሰህ አምጣ ተባልሁ።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
6 ጌታ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤የእስራኤል አምላክ ሆይ፤አንተን አጥብቀው የሚሹ፣ከእኔ የተነሣ አይዋረዱ።
7 ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፤እፍረትም ፊቴን ሸፍኖአልና።
8 ለወንድሞቼ እንደ ባዕድ፣ለእናቴም ልጆች እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
9 የቤትህ ቅናት በላችኝ፤የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ዐርፎአል።
10 ነፍሴን በጾም ባስመረርሁ ጊዜ፣እነርሱ ሰደቡኝ።