7 ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፤እፍረትም ፊቴን ሸፍኖአልና።
8 ለወንድሞቼ እንደ ባዕድ፣ለእናቴም ልጆች እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
9 የቤትህ ቅናት በላችኝ፤የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ዐርፎአል።
10 ነፍሴን በጾም ባስመረርሁ ጊዜ፣እነርሱ ሰደቡኝ።
11 ማቅ በለበስሁ ጊዜ፣መተረቻ አደረጉኝ።
12 በቅጥሩ ደጅ ለሚቀመጡት የመነጋገሪያ ርእስ፣ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ።
13 እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት፣ወደ አንተ እጸልያለሁ፤አምላክ ሆይ፤ በታላቅ ምሕረትህ፣በማዳንህም እርግጠኝነት መልስልኝ።