1 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤
2 አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል።
3 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣በደልም በእጄ ከተገኘ፣
4 በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣
5 ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ፤ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ