10 ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ በአንድ ላይ አሢረዋል፤
11 እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።
12 አምላክ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤አምላኬ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
13 ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።
14 እኔ ግን ሁል ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፤በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።
15 አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።
16 መጥቼ የጌታ እግዚአብሔርን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ፤የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።