1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤
2 እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።
3 ተራሮች ብልጽግናን፣ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።
4 ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤የድኾችን ልጆች ያድናል፤ጨቋኙንም ያደቀዋል።
5 ፀሓይ እስካለች ድረስ፣ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
6 እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል።
7 በዘመኑ ጽድቅ ይሰፍናል፤ጨረቃ ከስፍራዋ እስከምትታጣ ድረስም ሰላም ይበዛል።