7 በዘመኑ ጽድቅ ይሰፍናል፤ጨረቃ ከስፍራዋ እስከምትታጣ ድረስም ሰላም ይበዛል።
8 ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል።
9 የበረሓ ዘላኖች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ።
10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ግብር ያመጡለታል፤የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣እጅ መንሻ ያቀርባሉ።
11 ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።
12 ችግረኛው በጮኸ ጊዜ፣ምስኪኑንና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።
13 ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል።