9 የበረሓ ዘላኖች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም ዐፈር ይልሳሉ።
10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ግብር ያመጡለታል፤የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣እጅ መንሻ ያቀርባሉ።
11 ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።
12 ችግረኛው በጮኸ ጊዜ፣ምስኪኑንና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል።
13 ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል።
14 ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ደማቸውም በእርሱ ፊት ክቡር ነው።
15 ዕድሜው ይርዘም!ከዐረብ ወርቅ ይምጣለት፤ዘወትር ይጸልዩለት፤ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት።