1 እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው!
2 እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ።
3 ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4 አንዳች ጣር የለባቸውም፤ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው።
5 በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።
6 ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።