3 ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
4 አንዳች ጣር የለባቸውም፤ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው።
5 በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም።
6 ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል።
7 የሰባ ዐይናቸው ይጒረጠረጣል፤ልባቸውም በከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይፈስሳል።
8 በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ።
9 አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል።