8 በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ።
9 አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል።
10 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጒዳል፤ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ።
11 “ለመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል?በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?” ይላሉ።
12 እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ሁል ጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው።
13 ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል!
14 ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ጠዋት ጠዋትም ተቀጣሁ።