1 አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ስምህ ቅርብ ነውና ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ሰዎችም ስለ ድንቅ ሥራህ ይናገራሉ።
2 አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ።
3 ምድርና ሕዝቦቿ ሁሉ በሚናወጡበት ጊዜ፣ምሰሶቿን አጽንቼ የምይዝ እኔ ነኝ። ሴላ
4 እብሪተኛውን፣ ‘አትደንፋ’፤ክፉውንም ‘ቀንድህን ከፍ አታድርግ እለዋለሁ፤
5 ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር።’ ”