17 ደመናት ውሃን አንጠባጠቡ፤ሰማያት አንጐደጐዱ፤ፍላጾችህም ዙሪያውን አብለጨለጩ።
18 የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ተሰማ፤መብረቅህ ዓለምን አበራው፤ምድርም ራደች፤ ተንቀጠቀጠች።
19 መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ዱካህ ግን አልታወቀም።
20 በሙሴና በአሮን እጅ፣ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው።