5 የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ።
6 ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ከልቤም ጋር ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦
7 “ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን?ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን?
8 ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን?የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን?
9 እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ?ወይስ ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?።” ሴላ
10 እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።
11 የእግዚአብሔርን ሥራ አስታውሳለሁ፤የጥንት ታምራትህን በእርግጥ አስታውሳለሁ፤