1 ሕዝቤ ሆይ፤ ትምህርቴን ስማ፤ጆሮህንም ወደ አንደበቴ ቃል አዘንብል።
2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ፤
3 ይህም የሰማነውና ያወቅነው፣አባቶቻችንም የነገሩን ነው።
4 እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።