10 የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፤ በሕጉም መሠረት ለመሄድ እንቢ አሉ።
11 እርሱ የሠራውን ሥራ፣ያሳያቸውንም ድንቅ ነገር ረሱ።
12 አባቶቻቸው በዐይናቸው እያዩ፣በግብፅ አገር፣ በጣኔዎስ ምድር ታምራት አደረገ።
13 ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።
14 ቀን በደመና መራቸው፤ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን።
15 ዐለቱን በምድረ በዳ ሰነጠቀ፤እንደ ባሕር የበዛ ውሃ አጠጣቸው፤
16 ምንጭ ከቋጥኝ አፈለቀ፤ውሃን እንደ ወንዝ አወረደ።