19 እንዲህም ብለው በእግዚአብሔር ላይ ተናገሩ፤“እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድ ማሰናዳት ይችላልን?
20 ዐለቱን ሲመታ፣ ውሃ ተንዶለዶለ፤ጅረቶችም ጐረፉ፤ታዲያ፣ እንጀራንም መስጠት ይችላል?ሥጋንስ ለሕዝቡ ሊያቀርብ ይችላል?”
21 እግዚአብሔር ይህን ሲሰማ፣ እጅግ ተቈጣ፤በያዕቆብም ላይ እሳት ነደደ፤ቍጣውም በእስራኤል ላይ ተነሣ፤
22 በእግዚአብሔር አላመኑምና፤በእርሱም ማዳን አልታመኑም።
23 እርሱ ግን ከላይ ደመናትን አዘዘ፤የሰማይንም ደጆች ከፈተ፤
24 ይበሉም ዘንድ መና አዘነበላቸው፤የሰማይንም መብል ሰጣቸው።
25 ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፤ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው።