3 ይህም የሰማነውና ያወቅነው፣አባቶቻችንም የነገሩን ነው።
4 እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።
5 ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣አባቶቻችንን አዘዘ።
6 ይህም የሚቀጥለው ትውልድ እንዲያውቅ፣እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው፣ገና ለሚወለዱት እንዲነግሩ ነው።
7 እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም፤ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።
8 ነገር ግን እንደ አባቶቻቸው፣እልከኞችና ዐመፀኞች፣ልቡን ያላቀና፣መንፈሱም በእግዚአብሔር የማይታመን ትውልድ አይሆኑም።
9 የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።