30 ነገር ግን ገና ምኞታቸውን ሳያረኩ፣ምግቡ ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ፣
31 የእግዚአብሔር ቊጣ በላያቸው ላይ መጣ፤ከመካከላቸውም ብርቱ ነን ባዮችን ገደለ፤የእስራኤልንም አበባ ወጣቶች ቀጠፈ።
32 ይህም ሁሉ ሆኖ በበደላቸው ገፉበት፤ድንቅ ሥራዎቹንም አላመኑም።
33 ስለዚህ ዘመናቸውን በከንቱ፣ዕድሜአቸውንም በድንጋጤ ጨረሰ።
34 እርሱ በገደላቸው ጊዜ ፈለጉት፤ከልባቸው በመሻትም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
35 እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ልዑል አምላክ ቤዛቸው እንደሆነ አሰቡ።
36 ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤በአንደበታቸው ዋሹት።