55 ሕዝቦችን ከፊታቸው አባረረ፤ምድራቸውን ርስት አድርጎ አከፋፈላቸው፤የእስራኤልንም ነገዶች በጠላቶቻቸው ቤት አኖረ።
56 እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት፤በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ሥርዐቱንም አልጠበቁም።
57 ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ።
58 በኰረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቈጡት፤ተቀርጸው በተሠሩ ጣዖቶቻቸው አስቀኑት።
59 እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።
60 በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣የሴሎን ማደሪያ ተዋት።
61 የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።