56 እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት፤በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ሥርዐቱንም አልጠበቁም።
57 ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ።
58 በኰረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቈጡት፤ተቀርጸው በተሠሩ ጣዖቶቻቸው አስቀኑት።
59 እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።
60 በሰዎች መካከል ያቆማትን ድንኳን፣የሴሎን ማደሪያ ተዋት።
61 የኀይሉን ምልክት አስማረካት፤ክብሩንም ለጠላቶቹ እጅ አሳልፎ ሰጠ።
62 ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቈጣ።