7 እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም፤ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።
8 ነገር ግን እንደ አባቶቻቸው፣እልከኞችና ዐመፀኞች፣ልቡን ያላቀና፣መንፈሱም በእግዚአብሔር የማይታመን ትውልድ አይሆኑም።
9 የኤፍሬም ልጆች የታጠቁ ቀስተኞች ቢሆኑም፣በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።
10 የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፤ በሕጉም መሠረት ለመሄድ እንቢ አሉ።
11 እርሱ የሠራውን ሥራ፣ያሳያቸውንም ድንቅ ነገር ረሱ።
12 አባቶቻቸው በዐይናቸው እያዩ፣በግብፅ አገር፣ በጣኔዎስ ምድር ታምራት አደረገ።
13 ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።