1 አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ፤የተቀደሰውን ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ኢየሩሳሌምንም አፈራርሰው ጣሏት።
2 የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፣ምግብ አድርገው ሰጡ።
3 ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣እንደ ውሃ አፈሰሱ፤የሚቀብራቸውም አልተገኘም።
4 እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን።