3 ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣እንደ ውሃ አፈሰሱ፤የሚቀብራቸውም አልተገኘም።
4 እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው?የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን?ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
6 በማያውቁህ ሕዝቦች ላይ፣ስምህን በማይጠሩ፣መንግሥታት ላይ፣መዓትህን አፍስስ፤
7 ያዕቆብን በልተውታልና፤መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል።
8 የአባቶቻችንን ኀጢአት በእኛ ላይ አትቍጠርብን፤ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፤በጭንቅ ላይ እንገኛለንና።
9 አዳኛችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ስለ ስምህ ክብር ብለህ እርዳን፤ስለ ስምህ ስትል፣ታደገን፤ ኀጢአታችንንም ይቅር በል።