3 የጣቶችህን ሥራ፣ሰማያትህን ስመለከት፣በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣
4 በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5 ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው።
6 በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት፤
7 በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣የዱር አራዊትንም፣
8 የሰማይ ወፎችንና፣የባሕር ዓሦችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።
9 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!