6 ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግኸን፤ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን።
7 የሰራዊት አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።
8 ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ፤አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልሃት።
9 መሬቱን መነጠርህላት፤እርሷም ሥር ሰዳ አገሩን ሞላች።
10 ተራሮች በጥላዋ ተሸፈኑ፤ግዙፍ ዝግቦችም በቅርንጫፎቿ ተጠለሉ።
11 ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ፣ቊጥቋጦዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
12 ታዲያ ዐላፊ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲለቅም፣ለምን ቅጥሯን አፈረስህ?