1 አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ጭጭ አትበል።
2 ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ፣ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት።
3 በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።
4 “የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታወስ፣ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው” አሉ።
5 በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤በአንተም ላይ ተማማሉ፤
6 የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
7 ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤