15 እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤በማዕበልህም አስደንግጣቸው።
16 እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ፊታቸውን በዕፍረት ሙላው፤
17 ለዘላለም ይፈሩ፤ ይታወኩም፤በውርደትም ይጥፉ።
18 ስምህ እግዚአብሔር የሆነው አንተ ብቻ፣በምድር ሁሉ ላይ ልዑል እንደሆንህ ይወቁ።