5 በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ፤በአንተም ላይ ተማማሉ፤
6 የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣
7 ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር ሆነው ዶለቱ፤
8 አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤የሎጥ ልጆችም ረዳት ሆነ። ሴላ
9 በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።
10 እነርሱም በዐይንዶር ጠፉ፤እንደ ምድርም ጒድፍ ሆኑ።
11 መኳንንታቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣መሳፍንታቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤