1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን ወደ እኔ ጣል፤ ስማኝም፤እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና።
2 ለአንተ የተለየሁ ሰው ነኝና ነፍሴን ጠብቃት፤አንተ አምላኬ ሆይ፤በአንተ የታመነብህን ባሪያህን አድን።
3 ጌታ ሆይ፤ ማረኝ፤ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና።
4 የባሪያህን ነፍስ ደስ አሰኛት፤ጌታ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።