14 አምላክ ሆይ፤ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል፤የዐመፀኞችም ጉባኤ ነፍሴን ይሿታል፤አንተንም ከምንም አልቈጠሩም።
15 ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ለቊጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ።
16 ወደ እኔ ተመልከት፤ ማረኝም፤ለባሪያህ ኀይልህን ስጥ፤የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን።
17 የሚጠሉኝ አይተው ያፍሩ ዘንድ፣የበጎነትህን ምልክት አሳየኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ረድተኸኛልና፤ አጽናንተኸኛልም።