5 ጌታ ሆይ፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ነህ፤ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም።
6 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን አድምጥ፤የልመናዬን ጩኸት ስማ።
7 አንተ ስለምትመልስልኝ፣በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።
8 ጌታ ሆይ፤ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ከአንተም ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም።
9 ጌታ ሆይ፤ አንተ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ፣መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ፤ለስምህም ክብር ይሰጣሉ፤
10 አንተ ታላቅ ነህና፤ ታምራትም ትሠራለህ፤አንተ ብቻህን አምላክ ነህ።
11 እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤በእውነትህም እሄዳለሁ፤ስምህን እፈራ ዘንድ፣ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ።